ዩናይትድ፣ ኮቨንትሪ እና ቪላ የዛሬን ጨዋታ ያሸንፋሉ ብሏል ኦፕታ እናንተ ምን ያክል ትስማሙ ይኾን ይገምቱ?

0
20

በዛሬ 12ኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች

የጨዋታ ሰዓት ምሽት 12:00 ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

ምሽት 12:00 ሊድስ ዩናይትድ ከ ኮቨንትሪ

ምሽት 2:30 ኢፕስዊች ከ አስቶንቪላ ጋር ይጫዎታሉ።

ታሪካዊ ድል አልባ ጉዞ፦ ማንቸስተር ዩናይትድ በዘጠኝ ተከታታይ ጨዋታዎች ሳያሸንፍ በመቆየቱ በታሪኩ ረጅሙን ድል አልባ ጉዞ አስመዝግቧል። በሊጉም አንድ ድል ብቻ ነው ያሳካው (ከብቸኛ ድሉ በኋላ 90 ቀናት አልፈዋል)።

የመከላከል ድክመት፦ በሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለት እና ከዚያ በላይ ግቦች የተቆጠሩበት ሲኾን፣ ይህም ከ49 ዓመታት በኋላ የተከሰተ ደካማ አካሄድ ነው።

የአሠልጣኝ ፖቸቲኖ መግለጫ፦ በማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ስር ሦሥተኛ ጨዋታውን የሚያደርገው ዩናይትድ አሠልጣኙ ቡድኑን ለማሻሻል በጉጉት እየሠራ መኾኑን ቢገልጹም፣ መሻሻል ለማሳየት ጊዜ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ሁኔታና የቀደመ ግንኙነት፦

ማንቸስተር ዩናይትድ፦ በ8 ነጥብ 19ኛ ደረጃ (ወራጅ ቀጣና) ላይ ይገኛል። ኾኖም ብሬንትፎርድን በሜዳው ባደረጋቸው የመጨረሻ አምስት ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል።

ብሬንትፎርድ፦ በ17 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከሜዳው ውጪ ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ድል አላደረገም፤ ነገር ግን ከዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው የመጨረሻ ስድስት ጨዋታዎች በሁሉም ግብ አስቆጥሯል። በመጨረሻዎቹ ሦሥት ፍልሚያዎች ዩናይትድን ሁለት ጊዜ ያሸነፈ ሲኾን በእያንዳንዳቸው ሦሥት እና ከዚያ በላይ ግቦችን አስቆጥሯል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here