ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጡ አውሮፓዊ አጥቂ ተብሎ ተመረጠ።

0
66

ቢቢሲ ባዘጋጀው የሕዝብ ድምፅ አሰጣጥ መሠረት፣ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጡ አውሮፓዊ አጥቂ በመኾን ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል።

ቢቢሲ በመጀመሪያ 20 ታላላቅ አውሮፓዊ አጥቂዎችን በዕጩነት ካቀረበ በኋላ፣ በሕዝብ ድምፅ ምርጥ 10 ተጫዋቾች ተለይተው ወጥተዋል። በዚህም መሠረት ፈረንሳዊው ቲየሪ ሄንሪ ሁለተኛ እንዲሁም እንግሊዛዊው ሃሪ ኬን ሦሥተኛ ደረጃን በመያዝ ተከትለዋል።

በሕዝብ ድምፅ የተመረጡት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 አውሮፓዊ አጥቂዎች ደረጃ ስንመለከት፦

1ኛ ክርስቲያኖ ሮናልዶ

2ኛ ቲየሪ ሄንሪ

3ኛ ሃሪ ኬን

4ኛ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ

5ኛ ኤርሊንግ ሃላንድ

6ኛ ኪሊያን ምባፔ

7ኛ ዌይን ሩኒ

8ኛ ዝላታን ኢብራሂሞቪች

9ኛ ሩድ ቫን ኒስተልሮይ

10ኛ ካሪም ቤንዜማ

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here