የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች እና የስፖርት ተንታኝ ጋሪ ኔቪል፤ ኖርዌያዊው የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ኤርሊንግ ሃላንድ በመጨረሻ ክለቡን በመልቀቅ ወደ ስፔኑ ኀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ እንደሚያመራ ያለውን ግምትገልጿል።
ኔቪል ስለ ተጫዋቹ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሰጠው አስተያየት፤ ሃላንድ ቢበዛ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ወይም ምናልባትም በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ላይ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች እንደሚኾን ግምቱን አስቀምጧል።
አክሎም በሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ለውጥ ሲገልጽ፤ ብራዚላዊው ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል፣ ኪሊያን ምባፔ ወደ ግራ መስመር እንደሚመለስ እና ኤርሊንግ ሃላንድ የቡድኑ ዋና የፊት አጥቂ እንደሚኾን የተለያዩ ጠቋሚ መረጃዎች መሠረት አድርጎ ለስካይ ስፖርት ተናግሯል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



