‎ፊፋ በሳይበር ጥቃት የውስጥ መረጃዎቹ መሰረቃቸውን ገለጸ።

0
35

‎የዓለም እግር ኳስ አሥተዳዳሪ ፊፋ (FIFA) በሳይበር ጥቃት መጠቃቱን እና የግል እና የቢዝነስ መረጃዎቹ በሕገወጥ መንገድ መወሰዳቸውን ነው የገለጸው።

‎ፊፋ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በተፈፀመው የሳይበር ጥቃት በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ የግል እና የቢዝነስ መረጃዎች ተሰርቀዋል። ተቋሙ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር ጉዳዩን እያጣራ መኾኑንም አስታውቋል።
‎
‎የቢቢሲ የእግር ኳስ ጉዳዮች ዘጋቢ “ዴል ጆንሰን” እንደዘገበው ደግሞ ጥቃቱ በፊፋ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ወይም በሲስተም ብልሽት የተከሰተ አይደለም።
‎
‎ወንጀለኞቹ የተቋሙን ሠራተኞች በማስመሰል እና እነሱን በማታለል የሳይበር ጥቃቱን መፈፀማቸውን ነው የገለጸው።
‎
‎ለዚህ ወንጀል ‘Handsome Boy Hacking Club’ የተሰኘ የሳይበር ጠላፊዎች ቡድን ኀላፊነቱን ወስዷል።
‎
‎ቡድኑ 12 ጊጋባይት የሚደርስ የፊፋ መረጃ ማግኘቱን የገለጸ ሲኾን፣ ከዚህ ቀደምም የፊፋ ሰነዶችን የሚያሳዩ ምስሎችን በኢንተርኔት ላይ አጋርቶ እንደነበር አስታውሷል።
‎
‎ድርጊቱን ያወገዘው ፊፋ የግል መረጃዎችን በሕገ ወጥ መንገድ መውሰድ እና ማሰራጨት ከባድ መዘዝ የሚያስከትል ነው ብሏል ።
‎
‎ቢቢሲ የዓለም አቀፉ የእግርኳስ አሥተዳዳሪ ፊፋን ገልፆ እንደዘገበው የዓለም ዋንጫ የንግድ ድርሻን ለግል ባለሀብቶች የመሸጥ ሀሳብ ወይም የፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የዓለም ዋንጫ ሽያጭ ሴራ ተፈፀመ ከተባለው የሳይበር ጥቃት ጋር እንደማይገናኝ ገልጿል።

በባዘዘው መኮንን

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here