በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ምሽት 12:30 ላይ የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ ወደ አንፊልድ ተጉዞ ሊቨርፑልን ይገጥማል።
ማንቸስተር ሲቲ አምስቱንም ጨዋታዎች አሸንፎ በ15 ነጥብ ሊጉን ሲመራ፣ በሦሥት አቻ ውጤቶች 9 ነጥብ የሠበሠበው ሊቨርፑል 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ማንቸስተር ሲቲ በአንፊልድ ካደረጋቸው 29 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሦሥቱ ብቻ መኾኑ ታሪካዊ ፈተና ኾኖበት ቆይቷል።
በሊቨርፑል በኩል ኮዲ ጋክፖ እና አሌክሳንደር ኢሳክን ጨምሮ አምስት ተጫዋቾች በጉዳት አይሰለፉም።
በማንቸስተር ሲቲ በኩል ኤርሊንግ ሃላንድ እና አንቶይን ሴሜኒዮ ለዛሬው ጨዋታ ብቁ ሲኾኑ፣ ፊል ፎደን በቅጣት ከዚህ ጨዋታ ውጪ ኾኗል።
ቀን 10:00 ክሪስታል ፓላስ ከኖቲንግሃም ፎርስት እንዲሁም ሀል ሲቲ ከኤቨርተን የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የዕለቱ ሌሎች መርሐ ግብሮች ናቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



