የአብዩ ኤርሰሞ ስታዲየም የመጀመሪያው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ከባሕር ዳር ከተማ ያገናኛል።

0
28
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሲቀጥል ዛሬ ሀዲያ ሆሳዕናን ከባሕር ዳር ከተማ ያገናኛል።
ቡድኑን በአዲስ መልክ ያዋቀረው እና በአሠልጣኝ ደግአረገ ይግዛው የሚመራው የባሕር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ ድል ለማስመዝገብ ከሜዳው ውጭ አቅንቷል።
ጨዋታው ሀዲያ ሆሳዕና ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ በጀመረው የአብየ ሔርሳሞ ስታዲየም ይካሄዳል።
የጣና ሞገዶቹ ተጫዋቾች ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በቆይታቸውም ስድስት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን አድርገው አራቱን ሲያሸንፉ በአንዱ አቻ ወጥተዋል፤ በቀረው አንድ ጨዋታ ደግሞ ተሸንፈዋል።
ስኬታማ የሚባል የቅድመ-ውድድር ዝግጅት ጊዜ ያሳለፉት የጣና ሞገዶቹ ዓመቱን በድል ለመጀመር ወደ ሜዳ ይገባሉ።
ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ዓመት በደርሶ መልስ ጨዋታ ተገናኝተው ባሕር ዳር ከተማ ማሸነፉ ይታወሳል።
ጨዋታው ከሰዓት በኋላ በ9፡00 ይጀምራል።
በሌላ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከሸገር ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወታሉ።
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here