“ሰዎች ባስቆጠርኳቸው ግቦች ብቻ ሳይኾን ለወገኔ ባበረከትኩት በጎ ነገር እንዲያስታውሱኝ እፈልጋለሁ” ሳዲዮ ማኔ

0
60

 

ሳዲዮ ማኔ በትውልድ መንደሩ የ20 ሚሊዮን ዶላር የግብርና ፕሮጀክት አስጀመረ።

የሴኔጋሉ የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በትውልድ ቀዬው ባምባሊ “ኤስኤም10 አግሮ” የተሰኘ የ20 ሚሊዮን ዶላር የግብርና ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከ2ሺህ 500 በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ሲኾን ከ78ሺህ በላይ የማንጎ ዛፎችን ለመትከል ያለመ ነው።

ማኔ ከስኬቱ በስተጀርባ ያለውን ዓላማ ሲያብራራ “ከስቴዲየሙ መብራቶች እና ከእግር ኳስ ድሎቼ በፊት ባምባሊ ነበረች፤ ሰዎች ባስቆጠርኳቸው ግቦች ብቻ ሳይኾን ለወገኔ ባበረከትኩት በጎ ነገር እንዲያስታውሱኝ እፈልጋለሁ” ሲል መናገሩን ስካይ ስፖርት አስነብቧል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_15_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here