ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር የተሻሻለ የረጅም ጊዜ የውል ማራዘሚያ ስምምነት ላይ ደርሷል።

0
120

 

ይህ ስምምነት ክለቡን ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ክብር ካበቃ በኋላ ነው።

ምንም እንኳን አዲሱ ውል ለስንት ዓመታት እንደሚያቆየው በይፋ ባይረጋገጥም፣ አርቴታ በኤምሬትስ ስታዲየም ቢያንስ እስከ 10 ዓመት የሚያቆየው እንደሆነ ተገልጿል።

በአዲሱ ስምምነት መሰረት ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪ
ተዘጋጅቶለታል።

አርቴታ በዓመት 15 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚያገኝ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም ከቀድሞው የ10 ሚሊዮን ቋሚ ደመወዝ እና የ5 ሚሊዮን ፓውንድ የማበረታቻ ቦነስ ክፍያ ከፍ ያለ ነው።

የአርቴታ ውል በ2026/27 የውድድር ዘመን መጨረሻ ላይ የሚያበቃ ነበር። የክለቡ የበላይ ኃላፊዎች የበጋው የዝውውር መስኮት ከተዘጋ በኋላ የእሱን ውል ማደስ ዋነኛ ተግባራቸው አድርገውት ቆይተዋል።

ይህ ስምምነት አርሰናል በሀገር ውስጥ ሊግ እና በሻምፒዮንስ ሊግ ወሳኝ በሆነ ምዕራፍ ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በክለቡ የአመራር አካል ላይ የረጅም ጊዜ መረጋጋትን ይፈጥራል።

#አሚኮ #ስፓርት

#ባሕር_ዳር #መስከረም_12_2019_ዓ_ም

በዳናይት ሲሳይ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here