ኢትዮጵያውያኑ ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ብርቄ ኃየሎም በኮፐንሃገን የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ በ1ማይል ውድድር ለወርቅ ሜዳሊያ ይሮጣሉ።

0
128

 

በዴንማርክ ኮፐንሃገን ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና መክፈቻ በኾነው የሴቶች 1 ማይል ውድድር ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ብርቄ ሀየሎም ለድል ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የ1ማይል የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቅርቡ በላቲቪያ ሪጋ በአዲስ ቅርጽ ሲጀምር ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ኃይሉ ለኢትዮጵያ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ማስገኘታቸው ይታወሳል።

የዘንድሮውን የዳይመንድ ሊግ የ5000 ሜትር ፍጻሜ በአስደናቂ አጨራረስ በማሸነፍ የአጠቃላይ አሸናፊ የኾነችው ፍሬወይኒ ኃይሉ ከሪጋ የብር ሜዳሊያ በኋላ ሁለት ጊዜ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን በመኾን ለዚህ መድረክ ዝግጁነቷን አሳይታለች።

በሌላ በኩል በሻንጋይ፣ ስቶክሆልም እና ዶሃ የ1500 ሜትር ውድድሮችን ማሸነፍ የቻለችው ወጣት አትሌት ብርቄ ኃየሎም ከፍሬወይኒ ጋር በመኾን ለሀገሯ ተጨማሪ ድል ለማስመዝገብ የምትወዳደር ይኾናል።

48 አትሌቶች በሚሳተፉበት በዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ፍጥነት በሚጠይቀው ውድድር የፈረንሳይዋ አጋቴ ጊልሞት፣ የአሜሪካዋ አዲሰን ዊሊ እና የአውስትራሊያዋ ሳራ ቢሊንግስ ዋና ዋና ተፎካካሪዎች ናቸው።

የ27 ዓመቷ ፈረንሳዊት አጋቴ ጊልሞት በዓለም ሀገር አቋራጭ እና የቤት ውስጥ ውድድሮች ጥሩ አቋም ያሳየች ሲኾን አዲሰን ዊሊ እና ሳራ ቢሊንግስም በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ800 ሜትር ያስመዘገቧቸው የነሐስ ሜዳሊያዎች ለውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደርጋቸዋል።

የኮፐንሃገን የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና መክፈቻ የኾነው የሴቶች 1ማይል ውድድር መሥከረም 9/2019 ዓ.ም ረፋድ 5፡10 ላይ ይካሄዳል።

#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹

#አዲስ_አበባ #መስከረም_08_2019_ዓ_ም

በሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here