በሀገራችን እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ ትኩረት ከሚሹ ነገር ግን በክለቦች እና ባለድርሻ አካላት ችላ ከተባሉ ዘርፎች አንዱ የግብ ጠባቂነት ሙያ ነው።
በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከፍተኛ ሊግ ከሚወዳደሩ 18 ክለቦች መካከል 16ቱ የውጭ ሀገር ግብ ጠባቂዎችን የሚጠቀሙ መኾኑ የችግሩን ስፋት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ችግሩ የውጭ ሀገር ግብ ጠባቂዎችን ማስፈረም ላይ ብቻ ሳይኾን የመጡትስ ተጫዋቾች ለሀገር ውስጥ ግብ ጠባቂዎች ምን ያህል ልምድ አካፈሉ? የሚለው ጉዳይ በአግባቡ አለመታሰቡ ነው።
ይህንን ክፍተት ለመሙላት እና ላጋጠመው የግብ ጠባቂዎች እጥረት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት አሠልጣኝ አሻግሬ አድማሱ አዲስ ተስፋ ሰንቋል።
አሠልጣኝ አሻግሬ በባሕር ዳር ከተማ ታዳጊ ግብ ጠባቂዎች ብቻ ተለይተው የሚሰለጥኑበትን ልዩ ፕሮጀክት በመክፈት ፍሬያማ ሥራ ማከናወን ጀምሯል።
እነዚህ ታዳጊዎች የክለቦችን የውጭ ግብ ጠባቂ ጥገኝነት ለማስቀረት እና በራሳቸው ብቃት ለመተካት በትጋት በመለማመድ ላይ ይገኛሉ።
በቅርቡ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ታዳጊዎችን ሲመለምል በብቃት ካለፉት መካከል የዚሁ ፕሮጀክት አባላት ይገኙበታል።
ይህ ጥረት ተጠናክሮ ሲቀጥል እና ሌሎችም አካባቢዎች ትኩረት ተሰጥቶ ከተሠራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በሀገራችን እግር ኳስ የሚታየውን የግብ ጠባቂ ስጋት በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_06_2019_ዓ_ም
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



