ጄጄ ጋብሪኤል ከማንችስተር ዩናይትድ ለመውጣት ልምምድ አቋረጠ።

0
121
የ15 ዓመቱ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጫዋች ታዳጊ ጄጄ ጋብሪኤል ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን ተከተሎ ላለፉት ሦሥት ቀናት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሳይሠራ ከክለቡ ርቆ ይገኛል።
ታዳጊው ክለቡን ለቆ ለመውጣት የወሰነ ሲኾን የተጫዋቹ ወኪሎችም ከተለያዩ የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች የቀረቡለትን ጥያቄዎች እና ዝውውሮች እየገመገሙ ይገኛሉ።
ዩናይትዶች በበኩላቸው በክለቡ ከሚገኙ ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ታዳጊዎች አንዱ የኾነውን ጋብሪኤልን ለማቆየት የሚያስችል መፍትሔ ለማግኘት አሁንም ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጥረት ግን አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል ሲል ማርካ አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here