አርጀንቲናዊው የዕግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በስፔን ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሚወዳደረውን ሲዲ ኤልዴንሴ በሙሉ ባለቤትነት ለመግዛት
የሚያስችሉትን ይፋዊ ሰነዶች መፈረሙን ‘ማርካ ዘግቧል።
ስምምነቱ ባለፈው ሳምንት የተደረሰውን የቃላት ስምምነት ተከተሎ የተፈጸመ ሲኾን ሜሲ ለወደፊት የራሱን የክለቦች ሥብሥብ ለመገንባት ለያዘው ዕቅድ መነሻ እንደኾነ ተገልጿል።
ሂደቱ በስፔን ብሔራዊ የስፖርት ምክር ቤት ተገምግሞ ሲጸድቅ በሜሲ በኩል ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥበት ተጠቅሷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



