የዳይመንድ ሊጉ ጅማሮ
የፈረንጆቹ 2010 የአትሌቲክስ ውድድር እና የአትሌቶችን ግላዊ የድል እና የውድድር ብቃት ደረጃ ከፍ ያደረገ ዓመት ነው፡፡
15 ከተሞች ላይ የሚደረጉት ፉክክሮች መዳረሻቸው የሀገር ክብር፣ የድል አጥቢያ እና በዳይመንድ ያጌጠ ፈርጥ ከሺህ ዶላሮች ረብጣ ሽልማት ጋር ነው፡፡
26 ዓመታት በተሻገረው በዚህ መድረክም በርካቶች ነግሰዋል፡፡
በእነዚህ ዓመታት ከተከናወኑት መካከል አይረሴ የኾኑም አሉ፣ ከእነዚህ መካከል 6ቱን መለስ ብሎ ዲያመንድ ሊጉ አስታውሷል፡፡
በቀዳሚነት የምትጠቀሰው ኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕየጎን ናት፡፡
1ሺህ 500 ሜትር ባሕላዊ ድል እስከሚመስል ድረስ መንገስ ችላለች፡፡ ከ2021 አስከ 2024 ድረስ ባሉት ዓመታት በተከታታይ 4 ጊዜ የዳይመንድ ሊግ ፍጻሜ ባለድል በመኾን የሚስተካከላትም የለም፡፡
የርቀቱ ንግስት ብለው ብዙዎችም ይጠሯታል፡፡ኪፕዬጎን በመካከለኛ ርቀት ውድድር ላይ ያላትን የበላይነት በ2024ቱ የብራሰልስ ፍፃሜ ስታረጋግጥ ውድድሩን በ3 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ ከ75 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት የውድድሩን ክብረወሰን ሰብራለች፡።
5ኛውን የዳይመንድ ሊግ ዋንጫ በመሠብሠብ በሴቶች ውድድር ታሪክ ከፍተኛ የድል ዋንጫ ካላቸው ጥቂት ታላላቅ አትሌቶች መካከልም መኾን ችላለች፡፡
2ቱ አትሌቶች ያደረጉት ብዙውን ጊዜ ሲደጋገም የሚታይ አይደለም፡፡ በ2014 የዲያመንድ ሊጉ ፍጻሜ በከፍታ ዝላይ የኳታሩ ሙታዝ ኢሳ ባርሺም እና የዩክሬኑ ቦህዳን ቦንዳሬንኮ ያደረጉት ከፍተኛ ትንቅንቅ በመጨረሻም በአንዳቸው አሸናፊ በመኾን ተጠናቅቋል፡፡
ዓመቱን ሙሉ በተደረጉ ውድድሮች ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ ቆይተው የብራሰልስ ፍጻሜ ላይ ሲደርሱም
ዩክሬናዊው ቦህዳን ቦንዳሬንኮ በኒውዮርክ 2 ነጥብ 42 ሜትር በመዝለል የዳይመንድ ሊግ ክብረወሰን አስመዝግቦ ሲመጣ ለፈርጡ የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቶትም ነበር፡፡
ነገር ግን ሁለቱም አትሌቶች 2 ሜትር ከ40 ሴንቲ ሜትር በመዝለል አሸናፊውን ለመለየት ከፍታው ላቅ ብሎ ሲመጣ የኳታሩ ባርሺም በመጀመሪያ ሙከራው 2 ሜትር ከ43 ሴንቲ ሜትር በመዝለል አሸናፊ ኾኗል፡፡
በወቅቱም የዓለም የከፍታ ዝላይ ክብረወሰን የኾነ ነበር፡፡ በ1993 የፈረንጆቹ ዓመት የኩባው ሶቶማዮር 2 ሜትር ከ45 ሴንቲ ሜትር በመዝለል የዓለም ክብረወሰኑን በመከተል በ2ኛነት ተቀምጧል፡፡
ዳይመንድ ሊጉ ከተጀመረ በኋላ የመጀመሪያው የዓለም ክብረወሰን የተመዘገበው በአሜሪካዊው ኤሪስ ሜሪት አማካኝነት ነው፡፡
በፈረንጆቹ 2012 የዳይመንድ ሊጉ መቋጫ 110 ሜትር መሰናክልን በ12 ሰከንድ ከ80 ማይሮ ሰከንድ ድል በማድረግ የዓመቱ የዳይመንድ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ በመኾን ታሪክ ሠርቷል፡፡
ይህ ውጤት የቀደመውን የዳይሮን ሮብሌስን ክብረወሰን በነጥብ 07 ሰከንድ ያሻሻለ ሲኾን የሜሪት የወቅቱ የክብረወሰን ሰዓት ለ14 ዓመታት ያህል ሳይሰበር ቆይቶም ነበር፡፡
ከ2012 የሜሪት ሰዓት በኋላ ደግሞ በትላንትናው ዕለት የዓለም አትሌቲክስ ክብረወሰኑን ያጸደቀለት ጃኮብ ታርፕ በአሜሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ12 ሰከንድ ከ75 ማይክሮ ሰከንድ የርቀቱን ሰዓት እስኪያሻሽለው ድረስም አልተሰበረም ነበር።
በተጨማሪም አሜሪካዊቷ አትሌት ሳንዲ ሞሪስ በ2016ቱ የብራሰልስ ፍፃሜ የማይረሳ ታሪኳ ኾኗል፡፡ በምርኩዝ ዝላይ 5 ሜትር ከፍታ በመዝለል በታሪክ ሦሥተኛዋ ሴት አትሌት ኾናለች።
ራያን ክሩዘር፣ ጆ ኮቫክስ እና ቶም ዎልሽ በነበሩበት የ2017ቱ የአሎሎ ውርወራ ፉክክር የጠበቀው አልነበረም፡፡
ኾኖም መጨረሻ ላይ 22 ነጥብ 44 ሜትር በመወርወር የግል ምርጥ ውጤቱን አሻሽሎታል፡፡ ክፍ ሲልም የውድድሩ አዲስ ክብረወሰን ኾኖ ዓለምን አስደምሟል፡፡ ሲያጠናቅቅም የዳይመንድ ፈርጡን የግሉ አድርጓል፡
አስካሁን ድረስ ቅሬታ ከሚነሳባቸው ጉዳዮች መካከል የዳይመንድ ሊግ ውድድር በተከታታይ ቀናት እና በ2 የተለያዩ ከተሞች መኾኑ ነው፡፡ ይሄም የኾነው በፈረንጆቹ 2018 የውድድር ዓመት ነበር፡፡
ይሄንን ፈተና በስኬት ከተወጡት መካከል የኮሎምቢያዋ ካትሪን ኢባርጉየን አንዷ ናት፡፡ በ2 የተለያዩ ርቀቶች ማለትም በሱሉዝ ዝላይ እና በርዝመት ዝላይ ለፍጻሜ የሚያበቃ ውጤት ነበራት አትሌቷ፡፡
ከብራሰልስ ፍፃሜ ውድድር በፊት 1 ቀን ቀደም ብሎ ዙሪክ ላይ በሱሉዝ ዝላይ 14 ነጥብ 56 ሜትር በመዝለል 5ኛ የዳይመንድ ሊግ ክብርን ወሰደች፡፡ ወደ ብራሰልስ በሰዓታት ልዩነት በማምራት ደግሞ 6ሜትር ከ80 ሴንቲ ሜትር በርዝመት ዝላይ በመዝለል ድል አደረገች፡፡
ኢባርጉየን በሁለት ተከታታይ ምሽቶች፣ በሁለት የተለያዩ ከተሞች በመገኘት ሁለት የዳይመንድ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈች ብቸኛ አትሌት በመኾን በታሪክ ተመዝግባለች።
በ2 ቀናት ውስጥ 32 የፍጻሜ ውድድሮች ለዳይመንድ ፈርጡ እና ለ30 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሽልማት ገንዘብ በሚደረገው ፉክክር ዛሬስ ምን አዲስ ታሪክ እንመለከት ይኾን? ከሰዓታት በኋላ ምላሽ የምናገኝ ይኾናል፡፡
መረጃውን ከዲያመንድ ሊጉ ወሰድን፡፡
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_29_2018_ዓ_ም
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



