ፒትሶ ሞሲማኔ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ኾነው ተሾሙ፡፡

0
83
የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር የቀድሞ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና የአል አህሊ ዋና አሠልጣኝ የነበሩትን ፒትሶ ሞሲማኔን የባፋና ባፋና አዲስ ዋና አሠልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር ባደረገው አስቸኳይ ሥብሠባ የፒትሶ ሞሲማኔን ሹመት ማጽደቁን አስታውቋል፡፡
በቅርብ ወራት በተጠናቀቀው የዓለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካን የመሩት እና የአሠልጣኝነት ዘመናቸው የተጠናቀቀው አሠልጣኝ ሕጎ ብሩስን ኀላፊነት በመረከብ የብሔራዊ ቡድኑ አለቃ ይኾናሉ፡፡
የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ዳኒ ጆርዳን የኮሚቴው ውሳኔ ፒትሶ ሞሲማኔን ዳግም ወደ መንበሩ ለማምጣት ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውሰው የመጨረሻ ስምምነቶች ከተጠናቀቁ በኋላ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ትውውቅ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
አሠልጣኙ ለድጋሚ ኀላፊነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ከመምጣታቸው አስቀድሞ የኢራኑን እስተግላል ክለብን ለአንድ ዓመት አሠልጥነዋል፡፡
ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2012 ድረስ የደቡበ አፍሪካ ዋና አሠልጣኝ የነበሩት የ62 ዓመቱ ፒትሶ ሞሲማኔ በወቅቱ ባፋና ባፋናዎቹን በኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን ጥምረት በተሰናዳው የ2012ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማሳለፍ አለመቻላቸው ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እንዲለያዩ አድርጓቸዋል፡፡
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here