ማሊክ ፎፋና ከአርሰናል ይልቅ ሰንደርላንድን መርጧል፡፡

0
97
በተጫዋቾች ዝውውር ስሙ ከአርሰናል ጋር በስፋት ሲያያዝ የቆየው ቤልጅየማዊው የፊት መስመር ተጫዋች ማሊክ ፎፋና ወደ ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ሰንደርላንድ ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡
አርሰናል በሸጠው የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ ምትክ ለማድረግ ዝውውሩ ከመጠናቀቁ በፊት ተጨዋች እንደሚያመጣ ይጠበቃል፡፡
በዝውውሩም ልዩ ክትትል ሲያደርግበት የነበረውን የ21 ዓመቱ ማሊክ ፎፋና ከኦሎምፒክ ሊዮን ለማስፈረም ፍላጎት ማሳየቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ኾኖም ግን ሊዮን የጠየቀው የዝውውር ዋጋ 30 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ሲኾን አርሰናል ለመክፈል ፈቃደኛ ሳይኾን በመቅረቱ ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
የአርሰናልን ችላ ማለት ተከትሎ ወደ ዝውውሩ የገባው ሰንደርላንድ ፎፋናን ለማስፍረም ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡
ማሊክ ፎፋና ለሊዮን 83 ጨዋታዎችን አድርጎ 19 ግቦችን መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል፡፡
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here