ፉልሀም አልቫሮ አርቤሎአን በሦሥት ዓመት ኮንትራት አዲሱ አሠልጣኙ አድርጎ ሾሞታል።
ክለቡ የቀድሞው የሪያል ማድሪድ አለቃ የ43 ዓመቱ አርቤ ቤንፊካን ለመቀላቀል የተስማሙትን ማርኮ ሲልቫን በመተካት ነው የሾመው።
አርቤሎአ በሰጡት አስተያየት “አንጋፋ በኾነው ፉልሀም እግር ኳስ ክለብ ውስጥ ይህንን አዲስ ምዕራፍ በመጀመሬ ትልቅ ክብር ይሰማኛል” ብለዋል።
የክለቡ ሊቀመንበር ሻሂድ ኻን በበኩላቸው “አልቫሮ አርቤሎአ እራሱ እንደሚናገረው በጣም ታላቅ ምኞት ያለው ሰው ነው። በስፖርቱ ውስጥ ካሉ ምርጥ ተጫዋቾች፣ ክለቦች እና የአሠልጣኝነት ስልቶች ጋር ጥራት ያለው ጊዜ አሳልፏል፤ ይህም ተሞክሮ እዚህ ፉልሀም ውስጥ በደንብ ያገለግለዋል”ብለዋል።
“በተጨማሪም አልቫሮ አርቤሎአ በታዳጊዎች አካዳሚያችን ላይ ከፍተኛ ፍላጎት አለው፣ ለወጣት ተጫዋቾችም ዕድል በመስጠት ያምናል። ይህንን ከአልቫሮ በመስማቴ እና የማጥቃት አጨዋወት ለመተግበር ባለው ፍላጎት በጣም ተደስቻለሁ” ብለዋል።
አልቫሮ አርቤሎአ በጥር ወር ዣቢ አሎንሶ መልቀቁን ተከትሎ በጊዜያዊ አሠልጣኝነት ከመረከባቸው በፊት በማድሪድ የወጣቶች አሠልጣኝ ነበሩ።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የሪያል ማድሪድን 28 ጨዋታዎች የመሩት አሠልጣኙ በላሊጋው ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ደርሰዋል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ01_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



