የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ለ2026 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ፍጻሜ ጨዋታ አፍሪካዊ ዳኞችን መረጠ።

0
53
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር በኦስትሪያ ሳልዝበርግ የሚካሄደውን የፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና የአስቶን ቪላ ፍልሚያ እንዲመሩ ሦሥት የምሥራቅ አፍሪካ ዳኞችን መርጧል።
ይህ ውሳኔ በየአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር እና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መካከል የተፈረመውን የዳኞች ልምድ ልውውጥ ስምምነት ተከትሎ የተደረገ ሲኾን፣ በአውሮፓ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት ኾኖ ተመዝግቧል።
የየአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የዳኞች ኮሚቴ ሊቀመንበር ውሳኔውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ “ለ2026 የሱፐር ካፕ ጨዋታ ዳኞችን መምረጥ ማለት ለጨዋታው ታላቅነት የሚመጥን የክህሎት እና የፍትሐዊነት ደረጃን ማረጋገጥ ማለት ነው፤ ከካፍ ጋር በገባነው የትብብር ስምምነት መሠረት፣ ሶማሊያዊው ዳኛ ኦማር አርታንን እና ቡድኑን በመምረጣችን ኩራት ይሰማናል። ይህ ውሳኔ የዳኝነት ልምድ ልውውጥን ከማጠናከሩም በላይ፣ እግር ኳስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን አንድነት የሚያንጸባርቅ ነው።
ዳኞቹ በአፍሪካ መድረክ ላይ ያሳዩት ወጥነት እና በጨዋታ ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ለአውሮፓ መድረክም እጅግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል
ለዚህ ከፍተኛ ክብር የተመረጡት ዳኞች በአፍሪካ እግር ኳስ ዳኝነት ባላቸው ከፍተኛ ልምድ እና ብቃት የተመረጡ ናቸው።
የተመረጡት ዳኞችም፦
ዳኛ ኦማር አርታን ከሶማሊያ በዋና ዳኝነት
ዳኛ ሊባን አብዱልራዛክ አህመድ ከጅቡቲ 1ኛ ረዳት ዳኛ
ዳኛ ስቴፈን ይምቤ ከኬንያ 2ኛ ረዳት ዳኛ ኾነው ተመርጠዋል።
ዘጋቢ፦ ጥበቡ ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here