🏃‍♂️ ከማሸነፍ ባሻገር ለነጻነት የተከፈለ ዋጋ፤ የሐምሌ 5 መታሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ በሰቲት ሁመራ

0
7

 

ዝክረ ሐምሌ አምስት 10ኛ ዓመትን መነሻ በማድረግ በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ተካሂዷል።

ሐምሌ አምስት 2008 ዓ.ም ሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር አፍኖ ለመውሰድ ሞክሮ የተሸነፈበት ቀን ሲኾን በዞኑ በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ይታሰባል።

በዚህ መሰረት ይህ የእግር ኳስ ጨዋታ በሰቲት ሁመራ ከተማ አሥተዳደር ባሕል እና ስፖርት ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት የተካሄደ ሲኾን ዓለማው ከማሸነፍ እና መሸነፍ ባሻገር ለነጻ የተከፈለውን ዋጋ ለማሰብ መኾኑ ተገልጿል።

10ኛ ዓመትን የተሻገረው ቀኑ፤ በመንግሥት ሠራተኞች እና በባለሃብቶች መካከል በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ነው የታሰበው።

በሁለቱ ቡድኖች መካከል በተካሄደው በዚህ ጨዋታ የመንግሥት ሠራተኞች ተጋጣሚያቸውን 5 ለ3 በኾነ ውጤት አሸንፈዋል።

በላይ ሙሉጌታ የበላሃብቶች ቡድን ተጨዋች ሲኾኑ የዛሬው ጨዋታ ዓላማ የሐምሌ አምስትን የነጻነት ቀን ለማስቀጠል የተደረገ በመኾኑ ሁለቱም ቡድኖች አሸናፊ መኾናቸውን አንስተዋል።

ዓለሙ እያዩ ደግሞ የመንግሥት ሠራተኞች ቡድን ተጨዋች ናቸው። ጨዋታውን 5 ለ3 በኾነ ውጤት ማሸነፋቸው የቀኑ ማስታዋሻ መኾኑን አንስተው ቀኑ የነጻነት ችቦ የተለኮሰበት ስለመኾኑ አስረድተዋል።

የዞኑ ባሕል እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ አዳነች አለበል የቀኑ 10ኛ ዓመት በልዩ ኹኔታ እየተከበረ ይገኛል ብለዋል።

ስፖርት ለአንድነት እና ለትብብር ቁልፍ መሣሪያ መኾኑን በመገንዘብ መላው የዞኑ እና የክልሉ ሕዝብ አንድነቱን አንዲያጠናክር መልዕክት አስተላልፈዋል።

#ስፖርትለአንድነት #የነጻነትቀን #ኮሎኔልደመቀዘውዱ #Humera #Welkait #AmharaRegion
#ሁመራ #ሐምሌ4_2018_ዓ_ም

በአምሳሉ አሞኘ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here