አሠልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ኀላፊነት ለቀቁ።

0
59

 

#ባሕር_ዳር: ሰኔ 26/2018 ዓ.ም አሠልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ኀላፊነት መልቀቃቸው ተገልጿል።

በዓለም ዋንጫው በጊዜ የተሰናበተችው ጀርመን አሠልጣኟ ጋር ልትለያይ እንድምትችል ቀደም ሲል መገለጹ ይታወሳል። አሁን ላይ በወጣው መረጃ አሠልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን ከኀላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገልጿል።

ፋብሪዚዮ ሮማኖ ባወጣው መረጃ አሠልጣኙ ኀላፊነታቸውን ለቅቀዋል። በእርሳቸው ምትክ የቀድሞው የሊቨርፑል አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ እንደሚሾሙ ተገልጿል።

አሠልጣኝ የርገን ክሎፕ የሀገራቸውን ብሔራዊ ቡድን ለማሠልጠን ዝግጁ መኾናቸውም ተመላክቷል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here