🏆 በዓለም ዋንጫው የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች

0
276

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2018 ዓ.ም 🌏በ2026 የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ዛሬ ሦስት ተጠባቂ ጭዋታዎች ይደረጋሉ። የስፔን ብሔራዊ ቡድን ምሽት 4:00 ላይ ከኦስትሪያ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

የዓለም ዋንጫውን ያሸንፋሉ ተብለው ቅድመ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ስፔን በዛሬው ጨዋታ የምታሳየው አቋም ተጠባቂ ነው። ስፔን በምድብ ጨዋታዎች ኡራጋይ እና ሳውድ አረቢያን በማሸነፍ ከኪፕ ቨርዲ ጋር አቻ በመለያየት ምድቧን በአንደኝነት ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በሌላ ጨዋታ ፖርቹጋል ከክሮሽያ ይገናኛሉ።
በአንድ ወቅት በሪያል ማድሪድ ድንቅ ጥንዶች የነበሩት ክሪስቲያኖ ሮናልዶ እና ሉካ ሞድሪች በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ሀገራቸውን ወክለው በተቃራኒ ይገጥማሉ።

የሁለቱ ከዋክብት ፍጥጫ እና በጨዋታው ሊኖራቸው የሚችለው ብቃት ከወዲሁ አጓጊ ኾኗል። በሪያል ማድሪድ ስኬታማ የውድድር ዓመታት በጋራ ያሳለፉት ኮከቦቹ ለሀገራቸው ድንቅ ብቃትን ያሳዩ ይኾን? የሚለው በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል።

ኡዝቤኪስታንን አሸንፈው ከዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ እና ኮሎምቢያ ጋር አቻ በመውጣት 32ቱን የተቀላቀሉት ፖርቹጋሎች ከክሮሽያ ብርቱ ፈተና ይጠብቃቸዋል።

የቡድን የአንድነት መንፈሳቸው ደካማ እንደኾነ የሚነገርላቸው ፖርቹጋሎች ዛሬ ያንን ችግራቸውን ቀርፈው ይመለሱ ይኾን ? የሚለው አጓጊ ነው።

ክሮሺያዎች በምድብ ጨዋታዎች በእንግሊዝ ተሸንፈው ፓናማ እና ጋናን አሸንፈው ነው ለዛሬው ጨዋታ የደረሱት። ጨዋታው ሌሊት 8:00 ይካሄዳል።

በሌላ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስዊዘርላንድ ከአልጄሪያ ጠዋት 12:00 የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።

#አሚኮዜና# 🌏ዓለምዋንጫ#ስፖርት

በያየህ ፈንቴ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here