#አዲስ_አበባ: ሰኔ 26/2018 ዓ.ም በመጭው ነሐሴ/2018 ዓ.ም ላይ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት በሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት
በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ፣ ለመጻኢዎቹ የዓለም ኮከቦች የሚበረከቱት ማራኪ እና ልዩ ትርጉም ያዘሉ ሜዳሊያዎች ይፋ ተደርገዋል። 


በተፈጥሮ ውበቷ የምትታወቀው ኦሪገን፣ በሰሜን አሜሪካ በስፋቱ ትልቅ ከሚባሉት አንዱ የኾነው እና ለዘመናት የሀገሬው ተወላጆች የባሕል ማዕከል የነበረው የዊላሜት ፏፏቴ መገኛም ናት። 
ይህ ዲዛይን የተመረጠበት ምክንያት “በራሷ ክንፎች ትበራለች” የሚለው የኦሪገን ግዛት ታሪካዊ መፈክር በመኾኑ ነው። ይህ መፈክር በ1843 ዜጎቿ የራሳቸውን ጊዜያዊ መንግሥት ሲመሰርቱ በዳኛ ጄሲ ክዊን ቶርንተን የተጻፈ ነው።
በ1859 ኦሪገን ሙሉ በሙሉ የአሜሪካ ግዛት ስትኾን ለሀገሪቱ ታማኝነትን ለማሳየት ወደ “ኅብረቱ” ተቀይሮ ነበር። በ1987 ግን የግዛቲቱን ልዩ ማንነት እና የነዋሪዎቿን ቆራጥነት ለመግለጽ የቀድሞው ታሪካዊ መፈክር በሕግ ተመልሶ እንዲጸድቅ ተደርጓል።
ዛሬም ይህ አባባል በባሕላቸው ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነው፣ በተለይም ለሴቶች መብት ተሟጋቾች እና እንደ ፖርትላንድ ታውንስ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ ባሉ ተቋማት ላይ እንደ ማበረታቻ ያገለግላል። 

የብር ሜዳሊያው በቀይ እና ብርቱካናማ ሪባን ያለው ነው። ይህም ማራኪውን የማለዳ እና የምሽት የፀሐይ መውጫ እና መጥለቅ ቀለማትን ይወክላል። 
የነሐስ ሜዳሊያው ደግሞ በአረንጓዴ ሪባን ተደርጓል። ይህም የአካባቢውን አስደናቂ የተፈጥሮ ገጽታና ዕፅዋት ይገልጻል። 
ከዓለም አትሌቲክስ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሜዳሊያዎቹ በተጨማሪ በመድረኩ ተሳትፈው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በተመሳሳይ ዲዛይን የተዘጋጁ የክብር ፒኖችንም ይረከባሉ።
ይህ የ2026 የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ከ135 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ1ሺህ 700 የሚበልጡ አትሌቶችን ያሳተፋሉ። ኦሪገን ይህንን ታላቅ ውድድር ስታስተናግድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜዋ ነው።
በፈረንጆቹ 1986 “የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮና” በሚል በግሪክ የተጀመረው እና ከ2015 ጀምሮ ስያሜውን የቀየረው ይህ መድረክ፣ ዘንድሮ 21ኛ ውድድሩ ላይ ደርሷል።
ከሁለት ዓመት በፊት በፔሩ ሊማ በተካሄደው ውድድር 6 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በመሠብሠብ አሜሪካን ተከትላ በከፍተኛ ደረጃ ማጠናቀቋ ይታወሳል። 

የኢትዮጵያ የወደፊት የረጅም ርቀት እና የአጭር ርቀት ኮከቦችም አዲሱን “የክንፍ” ሜዳሊያ ለሀገራቸው ለማምጣት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ይኾናል። 


ዘጋቢ፦ ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



