ባሕር ዳር: ሰኔ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በስምንት ክለቦች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል የምዕራብ አማራ የቮሊቦል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቅቋል።
ሁለት እጁ እነሴ ከአዴት ከተማ ያደረጉት የዋንጫ ጨዋታ በአዴት ከተማ የቮሊቮል ክለብ 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል። አዴት ከተማ የውድድሩ የዋንጫ ባለቤትም ኾኗል።
ዳንግላ ከተማ እና ደቡብ አቸፈር ያደረጉት የደረጃ ጨዋታ በደቡብ አቸፈር 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ደቡብ አቸፈር የሦስተኛነት ደረጃን አግኝቷል።
በቀጣይም በምሥራቅ አማራ የሚገኙ ዞኖች እና ወረዳዎች መካከል የቮሊቮል ውድድር እንደሚካሄድ ታውቋል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
በዳናዊት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



