አዲስ አበባ: ሰኔ 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 42ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የ42 ኪሎ ሜትር የማራቶን ውድድር በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።
በወንዶቹ ከ230 በላይ አትሌቶች በተካፈሉበት ውድድር ገመቹ ያዴሳ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በበላይነት አጠናቅቋል።
አትሌት ባንተ መኮንን በተመሳሳይ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ አትሌት አሊ አቡ ከመቻል ሦሥተኛ ኾኖ ጨርሷል።
በሴቶቹ የመቻሏ አትሌት ጠጅቱ ስዩም በቀዳሚነት አጠናቅቃለች። አትሌት ከረኒ ጀሊላ ከኦሮሚያ ፓሊስ፣ አትሌት ትዕግሥት ጌትነት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሦሥተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
ለአሸናፊ አትሌቶቹ የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ከዋናው የአትሌቶቹ ፉክክር ባሻገር የማራቶን ውድድሩ በአንጋፋ አትሌቶች ዘርፍም ተደርጓል።
በአንጋፋዎቹ አትሌቶች ዘርፍ በወንድ ከ50 ዓመት በታች 1ኛ አትሌት በቀለ ረታ፣ 2ኛ አትሌት ቦጋለ ሰይፉ እና 3ኛ አትሌት አሰፋ መገርሳ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል።
ከ50 ዓመት በላይ ደግሞ አትሌት ገብረሊባኖስ ገብረ እግዚአብሔር፣ አትሌት አብደላ ሱሌይማን እና አትሌት አያሌው እንዳለ ከአንደኛ እስከ ሦሥተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል።
በሴቶች ኦሮሚያ ፖሊስ የዋንጫ አሸናፊ ኾኗል።
በወንዶች ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የዋንጫ አሸናፊ በመኾን አጠናቅቋል።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
ዘጋቢ:- ሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



