የ2026 የዓለም ዋንጫ ሌሊት የተካሄዱ ጨዋታዎች ውጤት

0
297

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ሌሊት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

ሞሮኮ ስኮትላንድን 1ለ0 አሸንፋለች። የማሸነፊያ ግቧን እስማኤል ሳይባሪ አስቆጥሯል።

ብራዚል ደግሞ ሀይቲን 3ለ0 ነው ያሸነፈችው። የማሸነፊያ ግቦቹን ማቲያስ ኩኛ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር እና ቪንሽየስ ጁኒየር ቀሪዋን ግብ አስቆጥሯል።

ሞሮኮ እና ብራዚል ነጥባቸውን አራት አድርሰዋል። በግብ ክፍያ ተበላልጠው ብራዚል አንደኛ እና ሞሮኮ ሁለተኛ ኾነው ምድቡን እየመሩ ነው።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here