ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ። በምድብ አንድ እና ሁለት የሚገኙ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች የቀጣይ ጉዟቸውን የሚወስኑ ተጠባቂ ፍልሚያዎችን ያደርጋሉ።
በመጀመሪያው ጨዋታቸው የተሸነፉት ቼክ ሪፐብሊክ እና ደቡብ አፍሪካ እርስ በእርስ ይገናኛሉ። ጨዋታው ምሽት 1፡00 ሰዓት ይካሄዳል።
ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ 2 ለ 0 በተሸነፈችበት ጨዋታ ሁለት ቁልፍ አማካዮቿን በቀይ ካርድ በማጣቷ ፈተና ውስጥ ወድቃለች። ቼክ ሪፐብሊክም በደቡብ ኮሪያ የደረሰባትን የ2 ለ 1 ሽንፈት ለማካካስ ዛሬ ወደ ሜዳ ትገባለች።
በዚሁ ምድብ ባለሦሥት ነጥቦቹ ሜክሲኮ እና ደቡብ ኮሪያ የምድቡን መሪነት ለመጨበጥ ሌሊት 10:00 እርስ በእርስ ይገናኛሉ።
ምድብ ሁለት ላይ አራቱም ብሔራዊ ቡድኖች እኩል አንድ አንድ ነጥብ አላቸው። ምሽት 4:00 ሰዓት ስዊዘርላንድ ጠንካራ መከላከል ከሚያሳየው ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና ጋር ብርቱ ፈተና ይጠብቃታል።
ሌሊት 7:00 ሰዓት ደግሞ ካናዳ ኳታርን ትገጥማለች።
የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



