ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዝውውር ገበያው ላይ የኦሳሱናውን ስፔናዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ቪክቶር ሙኖዝን በ40 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል።
ስካይ ስፖርት እንደዘገበው ከኾነ ሊቨርፑል ተጫዋቹን ፈልጎት የነበረውን የኒውካስል ዩናይትድን ጥረት ሙሉ በሙሉ በማክሸፍ የውል ማፍረሻ የኾነውን 34 ነጥብ 6 ሚሊዮን ፓውንድ ለኦሳሱና ለመክፈል ወስኗል።
በሳሙኤል ጥሩነህ (ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



