ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ዋንጫ የምድብ ጄ ጨዋታ አርጀንቲና አልጄሪያን 3 ለ 0 በኾነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች።
በዚህ ጨዋታ የአርጀንቲናዎች ምሰሶ ሊዮኔል ሜሲ በ17ኛው፣ በ60ኛው እና በ76ኛው ደቂቃ ላይ ግብ በማስቆጠር ሀትሪክ ሠርቷል።
በሌላ ሌሊት 7:00 ላይ በተካሄደ ጫዋታ የኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ከኢራቅ ጋር የነበረውን የምድቡን የመጀመሪያ ውድድር በድል ተወጥቷል። የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኘው ሀላንድ 2 ግቦችን አስቆጥሯል። ቀሪ ግቦችን ሊዮ ኦስቲጋርድ እና አይመን ሁሴን (በራሱ ላይ) ግብ አስቆጥሯል።
ለኢራቅ ብቸኛዋን ግብ አሕመድ ሁሴን በግምባሩ ገጭቶ አግብቷል። ውጤቱም 4ለ1 በኾነ ውጤት ተጠናቅቋል።
#አሚኮ_ዜና # ስፖርት_የዓለም_ዋንጫ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



