ሩበን አሞሪም የኤሲ ሚላን አሠልጣኝ ለመኾን ተስማሙ።

0
6

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም የኤሲ ሚላን አሠልጣኝ ለመኾን መስማማታቸው ተገልጿል።

ኤሲ ሚላን ሩብን አሞሪምን ዋና አሠልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከአሠልጣኙ ጋር መስማማቱን ፋብሪዞ ሮማኖ ዘግቧል። አሠልጣኙ እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር እስከ 2028 ድረስ የሚያቆይ ውል እንደሚፈርሙ ይጠበቃል።

ስምምነቱን እስከ 2029 ማራዘም የሚያስችል አማራጭ እንደሚኖርም ተገልጿል።

አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም ከማንቸስተር ዩናይትድ አሠልጣኝነት ከተሰናበቱ በኋላ ያለ ሥራ መቆየታቸው ይታወሳል።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here