ኩኩሬላ በይፋ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ኾኗል።

0
5

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ እግር ኳስ የዝውውር መስኮት መከፈቱን ተከትሎ ስሙ ከሪያል ማድሪድ ጋር ሲነሳ የቆየው ስፔናዊው የግራ መስመር ተከላካዩ ማርክ ኩኩሬላ የቼልሲ ቆይታውን አጠናቅቆ የሳንቲያጎ በርናባውን ቤት በይፋ ተቀላቅሏል።

ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹ በክለቡ ቤት እስከ 2032 ድረስ የሚያቆየውን የረጅም ጊዜ ውል በይፋ ተፈራርሟል። ተጫዋቹ የሉስብላንኮሶቹን የረጅም ጊዜ ዕቅድ እና የተከላካይ ክፍላቸውን ለማጠናከር ይረዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጫዋቹ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያለውን የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ እንዳጠናቀቀ ዝውውሩ ይፈጸማል ተብሏል።

በተከላካይነት ላይ በክንፍ ማጥቃት ተሳትፎው እና በጉልበቱ የሚታወቀው ኩኩሬላ በካርሎ አንቸሎቲ ስብስብ ውስጥ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ስካይ ስፖርት እና ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብበዋል።

በሳሙኤል ጥሩነህ (ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here