በዓለም ዋንጫው አፍሪካን ከሚወክሉት መካከል ሶማሊያዊው ዳኛ የአሜሪካን ምድር እንዳይረግጡ ተከለከሉ።

0
15
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዘንድሮውን የ2026 የዓለም ዋንጫ በበላይነት ለመምራት ከተመረጡት 52 የፊፋ ዋና ዳኞች መካከል አንዱ የኾኑት ሶማሊያዊ ዳኛ ዑመር አርታን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተረጋግጧል።
ዳኛ ዑመር አርታን ደቡብ ፍሎሪዳ ማያሚ ቢደርሱም የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት “በደኅንነት ማጣራት ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ብቁ ኾነው አልተገኙም” በሚል ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መከልከሉን እና ውሳኔውም መጽናቱን ለአልጀዚራ በላኩት ኢሜይል አረጋግጠዋል።
ይህ ውሳኔ አሜሪካ ከዓለም ዋንጫው ጋር በተያያዘ የጣለችውን የጉዞ ገደብ እና የቪዛ አሰጣጥ ፖሊሲ በተመለከተ ከፍተኛ ትችት እና ስጋት እየቀሰቀሰ ይገኛል።
ዳኛ ዑመር አርታን በዓለም ዋንጫ ታሪክ ጨዋታ ለመምራት ዕድል ያገኙ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ በመኾን ታሪክ ለመሥራት ተቃርበው የነበረ ቢኾንም በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሥተዳደር ሶማሊያን ባካተተው የጉዞ እገዳ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ እየተሰናዳ ይገኛል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here