ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ከ32 ወደ 48 ከፍ ማለቱን ተከትሎ አጠቃላይ የጨዋታዎች ብዛት ወደ 104 አድጓል።
ይህ አዲስ አሠራር የጥሎ ማለፍ ደንቡን ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።
የምድብ ድልድል እና የ32ቱ ዙር ማለፊያ ደንብ፦
👉 48ቱ ሀገራት በ12 ምድቦች ማለትም በእያንዳንዱ ምድብ 4 ቡድኖች ይከፈላሉ።
👉 ከየምድባቸው 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ 24 ቡድኖች በቀጥታ ወደ 32ቱ ዙር ያልፋሉ።
👉 ከየምድባቸው 3ኛ ኾነው ከሚያጠናቅቁት 12 ሀገራት መካከል ምርጥ 8 ቡድኖች ተለይተው የጥሎ ማለፉን ይቀላቀላሉ። በምድብ 4ኛ የኾኑት ግን በቀጥታ ይሰናበታሉ።
👉 ምርጥ 3ኛ የወጡ 8 ቡድኖችን ለመለየት የሚጠቅሙ መስፈርቶች
ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ቅድሚያ ያገኛሉ። ነጥብ እኩል ከኾነ ደግሞ የተሻለ የግብ ልዩነት ያላቸው ያልፋሉ። የግብ ልዩነቱም እኩል ከኾነ ብዙ ግብ ያስቆጠረ ቡድን ይመረጣል።
ከላይ የተጠቀሱት እኩል ከኾኑ አነስተኛ የካርድ ነጥብ ያለው ያልፋል። ይህም ቢጫ ካርድ 1 ነጥብ፣ በሁለት ቢጫ ቀይ 3 ነጥብ፣ ቀጥታ ቀይ 4 ነጥብ፣ ቢጫ እና ቀጥታ ቀይ 5 ነጥብ።
እንደ ፊፋ ዶት ኮም መረጃ ካርዳቸውም እኩል ከኾነ በፊፋ የዓለም የደረጃ ሰንጠረዥ ከፍ ብሎ የሚገኘው ሀገር ያልፋል።
የ32ቱ ዙር የጨዋታ ድልድል
ከምድባቸው በ3ኛነት የሚያልፉት 8ቱ ሀገራት ከ8ቱ የምድብ አሸናፊዎች ጋር ይገናኛሉ።
የቀሩት 4ቱ የምድብ አሸናፊዎች በምድባቸው 2ኛ ከወጡ 4 ሀገራት ጋር ይጫወታሉ።
የቀሩት 8ቱ ሁለተኛ የወጡ ሀገራት እርስ በርሳቸው በቀጥታ ይፋለማሉ።
#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_እግር_ኳስ
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



