አትሌት ዓለምናት ዋለ አሸነፈች።

0
5

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ በሰጠው በቱርኩ ፊንላንድ በተካሄደው ኮንቲኔንታል ቱር የ2026 የፓቮ ኑርሚ ውድድር አትሌት ዓለምናት ዋለ አሸንፋለች።

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር አትሌት ዓለምናት ዋለ 9 ደቂቃ 16 ሰከንድ 18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው በአንደኝነት ያሸነፈችው።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ደግሞ አትሌት አብርሃም ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ማሸነፍ ችሏል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_አትሌቲክስ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here