የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ድሉ ለማን ይኾን ?

0
7

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ቀን 11:00 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በማንቼስተር ሲቲ እና በቼልሲ መካከል ይደረጋል።

ጨዋታውን እንግሊዛዊው ዳኛ ዳረን ኢንግላንድ በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።

በፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንቼስተር ሲቲ ሳውዛምፕተንን 2ለ1 አሸንፎ ለፍጻሜ የበቃ ሲኾን የዘንድሮውን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት ለፍጻሜ መድረስ ችሏል። አስቀድሞ የካራባኦ ዋንጫን ያሳካው እና በሊጉም የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሲቲ ዛሬ ስምንተኛ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫውን በማንሳት የሦሥትዮሽ ድል (ትሪፕል) ጉዞውን ለማጠናከር ወደ ሜዳ ይገባል። ክለቡ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳው በ2023 ነበር።

ተጋጣሚው ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1ለ0 አሸንፎ ለፍጻሜ የደረሰ ሲኾን የውድድር ዓመቱን ያለምንም ዋንጫ ላለማጠናቀቅ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል።

በታሪኩ 8 ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ ሻምፒዮን የኾነው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለ9ኛ ጊዜ ለማሸነፍ የሚጫወት ሲኾን ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳው በ2018 ነበር።

በውድድሩ ታሪክ አርሰናል 14 ጊዜ፤ ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ 13 ጊዜ በማሸነፍ ቀዳሚዎቹ ናቸው።

በምስጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here