ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል።

0
6

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 32ኛ ሳምንት ጨዋታ በዛሬ ሦሥት ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።

ከዛሬ ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው። ፋሲል ከነማ በደረጃ ሠንጠረዡ በ43 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በ38 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አዳማ ከተማ ጋር ነው ብርቱ ፉክክር የሚያደርገው።

በ31ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ሽንፈት የገጠመው ፋሲል ከነማ ዛሬ ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው።

ጨዋታው በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ምሽት 12፡00 ላይ ይደረጋል። በዚህ ጨዋታ ፋሲል ከነማ በደጋፊው ፊት ከሚጫወተው አዳማ ከተማ ጠንካራ ፉክክር ይጠብቀዋል።

ሌሎች የሊጉ ጨዋታዎችም ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ 9፡00 ላይ በአዲስ አበባ አበበ ቢቄላ ስታዲየም ጨዋታውን ሲያደርግ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here