በላንክሻየር ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ይፋጠጣሉ።

0
80

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ሊቨርፑልን ምሽት 11:30 ላይ ያስተናግዳል።

ሁለቱ ታሪካዊ ባላንጣ ክለቦች የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።

ዩናይትድ በካሪክ ሥር ከኾነ አንስቶ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል።

በ2026 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዩናይትድ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ ያልተሸነፈ ክለብ መኾኑ ቡድኑ ለውጥ የማምጣቱ ማሳያ ነው።

በዚህ ዓመት ግንኙነታቸው ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ አንፊልድሮድ አቅንቶ 2ለ1 በኾነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

በሌላ መርሐ ግብር በርንማውዝ ከክርስቲያል ፓላስ ቀን 10:00 ላይ ይገናኛሉ።

የመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ቶትንሃም ሆትስፐር ወደ ቪላ ፓርክ አቅንቶ አስቶንቪላን ምሽት 3:00 ላይ ይገጥማል።

በላንክሻየር ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ማን የሚያሸንፍ ይመስልዎታል?

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here