ማንቸስተር ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ ዛሬ ይጫዎታል።

0
51

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ምሽት 4፡00 ላይ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከኾነ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ይዞ ለማጠናቀቅ የሚያደርገውን ጉዞ ያሳምራል።

ብሬንትፎርድ ለማንቸስተር ዩናይትድ ብርቱ ተፎካካሪ ኾኖ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ሁለቱ ክለቦች በሊጉ እርስ በእርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለቱም ሁለት ሁለት ጊዜ ድል ሲያደርጉ በቀሪው አንድ ጨዋታ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በሊጉ ማንቸስተር ዩናይትድ በ58 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ነው። ብሬንትፎርድ ደግሞ በ48 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here