ኮቢ ሜይኖ በማንቸስተር ዩናይትድ ለመቆየት ተስማማ።

0
25

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 13/2018 (አሚኮ) ወጣቱ የካሪንግተን ምሩቅ ኮቢ ሜይኖ በማንቸስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት የሚያቆየውን የውል ስምምነት ለማራዘም ከቃል ስምምነት ላይ ደርሷል።

በአሠልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር የቡድኑ የዐይን ብሌን የኾነው ሜይኖ በሳምንት ይከፈለው የነበረው 25 ሺህ ፓውንድ ወደ 150 ሺህ ፓውንድ ከፍ እንደሚልለትም ተገልጿል።

ዩናይትድ የውድድር ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት ስምምነቱን በይፋ እንደሚያበስር ይጠበቃል።

ይህ ውሳኔ በሩበን አሞሪም ዘመን ተፈጥሮ የነበረውን የመልቀቅ ወሬ ሙሉ በሙሉ የገታ ስለመኾኑ ስካይ ስፖርት እና ያሆ ስፖርት አስነብበዋል።

በአድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here