አዲስ አበባ: ሚያዚያ 13/2018 (አሚኮ) የዓለም አትሌቲክስ የዱላ ቅብብል ውድድር (World Athletics Relays) በ2026 ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ይካሄዳል።
ደቡብ አፍሪካዊቷ ቦትስዋና በዋና ከተማዋ ጋቦሮኒ ከ40 ሀገራት የተውጣጡ 723 ፈጣን አትሌቶችን ለማስተናገድ የመጨረሻ ዝግጅቷን አጠናቅቃለች።
ከግንቦት 02/2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ 8ኛው መድረክ ላይ የኦሎምፒክ ኮከቡ ሌትሲል ቴቦጎ ቦትስዋናን በመምራት በደጋፊው ፊት ለድል ይሮጣል።
እንደ አሜሪካ፣ ጃማይካ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ የአጭር ርቀት ኀያላን ሀገራትም በሮኒ ቤከር እና አካኒ ሲምቢኔ በሚመሩ ጠንካራ ሥብሥቦቻቸው ይሳተፋሉ።
ኢትዮጵያም በሁለት ዘርፎች ትሳተፋለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲኾን ውድድሩ ለቀጣይ ዓለም አቀፍ መድረኮች የማለፊያ ትኬት የሚቆረጥበት በመኾኑ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል።
ኢትየጰያም በድብልቅ 4*400 እና በሴቶች 4*400 ነው የምትሳተፈው።
በወንዶች 4*400 ሜትር ድብልቅ
ኢሪማ ቀሬ
ኒያል ኒያንግ
መርዶክዮስ ወልዴ
አጃይባ አልዩ
ባንቻለም ቢክስ
ባንቻየሁ ተሰማ
በሴት 4*400
አጃይባ አልዬ
ገነት አየለ
ራሄል ተስፋዬ
ባንቻለም ቢክስ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።
እስካሁን ባሉት ሰባት ውድድሮች አሜሪካ በ38 ሜዳሊያዎች የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራች ትገኛለች። አፍሪካ በዓለም አቀፍ ስፖርት ያላትን አቅም የምታሳይበት ይህ ታሪካዊ መድረክ በጉጉት እየተጠበቀም ይገኛል።
በሀናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



