ባሕር ዳር: ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ማንቸስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለመቅረፍ ከበርንለይ ጋር ይጫወታል።
በወረጅ ቀጣና ላይ የሚገኘው በርንለይ በሜዳው ማንቸስተር ሲቲን የሚያስተናግድ ሲኾን ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ሲቲ ጨዋታውን ካሸነፈ ነጥቡን ከአርሰናል ጋር ዕኩል 70 ነጥብ በማድረስ ይበልጥ የዋንጫ ፉክክሩን ያሳድጋል።
በተመሳሳይ ምሽት 4:00 ላይ በርንማውንዝ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይገናኛሉ።
ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው በርንማውንዝ ጨዋታውን ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ስድስተኛ የሚያሳድግ ይኾናል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



