ተጠባቂው ፉክክር በኢትሃድ ስታድየም!

0
9

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በ33ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ ከአርሰናል የሚያደርጉት ብርቱ ፉክክር ዛሬ ተጠባቂ ነው።

አርሰናል ዋንጫ የሚያነሳበትን ዕድል ከፍ ለማድረግ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ልዩነቱን ለማጥበብ እና የዋንጫ ግስጋሴውን ለማጠንከር ነው የሚፋለሙት።

ሊጉን በስድስት ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው አርሰናል ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ያስመዘገበው ውጤት ደካማ ነው።

አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ባለፉት አምስት ውድድሮች ጥሩ አቋም ታይቶበታል። ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ በሜዳቸው ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጨዋታው በኢትሃድ ስታዲየም ምሽት 12:30 ይጀምራል።

አርሰናል ሊጉን በ70 ነጥብ ሲመራ ቀሪ አንድ ጨዋታ ያለው ማንቸስተር ሲቲ በ64 ነጥብ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይከተላል።

ከማንቸስተር ሲቲ እና ከአርሰናል ጨዋታ በፊት አስቶንቪላ ከሰንደርላንድ፣ ኖቲንግሃም ከበርንለይ 10:00 ላይ የሚገናኙ ሲኾን በተመሳሳይ ሰዓት በመርሲሳይድ ደርቢ ደግሞ ኤቨርተን በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናግዳል።

በያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here