ባሕር ዳር: ሚያዝያ 11/2018 (አሚኮ) እ.አ.አ 2026 በሞሮኮ አስተናጋጅነት የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ዛሬ በሀገራቸው ሜዳ ያስተናግዳሉ።
የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ጨዋታውን 2ለ0 አሸንፎ የመጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የመልሱን ጨዋታ ያደርጋል።
በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የሚጫዎተው ከ17 ዓመት በታች የሴቶች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የተሻለ ውጤት እንደሚያስመዘግብም ይጠበቃል።
ጨዋታው በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ቀን 10:00 ላይ ይደረጋል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !



