ፋሲል ከነማ ዛሬ ደረጃውን ለማሻሻል ይጫወታል።

0
18

 

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ሲጀመር ሁለት ጨዋታ ይካሄዳሉ።

ፋሲል ከነማ ከመቀለ 70 እንደርታ ጋር ከቀኑ 9፡00 ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ፋሲል ከነማ በ42 ነጥብ እና በአራት የግብ ክፍያ አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲኾን የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ከኾነ ሌሎች ጨዋታዎች እስከሚደረጉም ቢኾን ነጥቡን 45 በማድረስ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ የሚልበትን ዕድል ያመቻቻል።

ፋሲል ከነማ በ27ኛ ሳምንት ጨዋታው ከወላይታ ዲቻ ጋር ተገናኝቶ 1ለ0 ያሸነፈ በመኾኑ ለዚህኛው ጨዋታ የተሻለ ሥነ ልቦና ይዞ እንዲገባ ያስችለዋል።

በአንጻሩ መቀለ 70 እንደርታ ባለፈው የሊጉ ሳምንት ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2ለ1 ያሸነፈ በመኾኑ ለፋሲል ከነማ ቀላል ቡድን እንደማይኾን መረጃዎች ያሳያሉ።

ይሁን እንጅ መቀለ 70 እንደርታ በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ግርጌ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ በ26 ነጥብ የተቀመጠ ክለብ መኾኑ ክለቡ በየጊዜው የሚቀያየር አቋም እንዳለው ያሳያል። ይህም ፋሲል ከነማ ጨዋታውን ለማሸነፍ የሚችልበት ዕድል እንዳለው ያሳያል።

በሊጉ የዛሬው ሌላኛው ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ምሽት 12፡00 ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚያደርጉ ጨዋታ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here