የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫውን መዳረሻ ወደሚጠቁመው ወሳኝ ምዕራፍ ደርሷል።

0
68
ባሕር ዳር ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ይደረጋሉ። በዋንጫ ፉክክሩ ከአንድ ጨዋታም በላይ ትርጉም ባለው መርሐ ግብር ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን ያስተናግዳል።
ሊጉን አርሰናል በ70 ነጥብ ይመራል። ማንቸስተር ሲቲ በ64 ይከተላል። በመካከላቸው የ6 ነጥብ ልዩነት አለ። ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲ ቀሪ ጨዋታ አለው።
በመኾኑም ማንቸስተር ሲቲ ከአርሰናል ጋር ያለውን ጨዋታ እና ተስተካካዩን ካሸነፈ ነጥባቸው ዕኩል ይኾናል።
ለዚህ ደግሞ ማንቸስተር ሲቲ ጥሩ የሥነ ልቦና ግንባታ ታሪኮች እና እውነታዎች አሉት። ከእነዚህ መካከል ማንቸስተር ሲቲ እና አርሰናል በኢትሀድ ባለፋት 10 ጨዋታዎች የፔፕ ቡድን አልተሸነፈም እንዳውም በ7ቱ አሸንፏል።
በቅርቡም በሜዳው ከሁሉም ክለቦች ጋር ባደረጋቸው የቅርብ 14 ጨዋታዎች አልተሸነፈም። ወርሐ ሚያዚያ ለጋርዲዮላ የስኬት ወር ነው። ከየትኛውም ወር በላይ በአሠልጣኝነት ዘመኑ የማሸነፍ ምጣኔው ከፍ ያለበት ነው።
ከየ ጨዋታዎች ከ2 ነጥብ 5 በላይ ነጥብ የማግኘት እና 80 በመቶ አካባቢ የማሸነፍ ንጽጽርም አለው።
በአንጻሩ አርሰናል በሚኬል አርቴታ እየተመራ ደካማ የውጤት ምጣኔው በሚያዝያ ወር ነው። 42 በመቶ አካባቢ አሸንፏል።
በሌላ በኩል ግን የአርሰናል እርስ በርስ ግንኙነት 92 ለ 58 በመቶ የግንኙነት ታሪክ ብልጫ መኖሩ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ በፕሪምየር ሊጉ በቅርብ የአምስት ጨዋታ ግንኙነታቸው አርሰናል አለመሸነፉ ብርታት ይኾነዋል።
ጨዋታው እሑድ 12:30 ይጀምራል።
አርሰናል ካሸነፈ የዋንጫ መዳረሻው ወደ መለየቱ ይቃረባል። ማንቸስተር ሲቲ ከረታ ግን የዋንጫ ፋክክሩ የበለጠ አጓጊ ይኾናል።
ዘጋቢ፦ መለሰ ግዛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here