
የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ዘመናዊነትን ከታሪካዊ ይዘት ጋር ያጣመረ፣ የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ እና በሞዴልነት የሚወሰድ ሥራ መኾኑን የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አብዱላሒ አደን ገልጸዋል።
ከንቲባ አብዱላሒ አደን በሀረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን እና የጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ በጀጎል ጥንታዊ ከተማ የተካሄደው የኮሪደር ልማት በአነስተኛ ወጪ የቅርሱን ደኅንነት እና ታሪካዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ ተከናውኗል።
ይህም የከተማዋን ሁለንተናዊ የመስህብ እሴቶች አጉልቶ ከማሳየቱ ባለፈ፣ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የሚያግዝ እና ለምሥራቅ ኢትዮጵያ በሞዴልነት የሚወሰድ ሥራ መኾኑን ተናግረዋል።
ከንቲባው በጉብኝታቸው የጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ መንገዶች እና የአንደኛ መንገድ የእግረኛ መሄጃ ኮሪደር ልማቶችን ጨምሮ፣ የበድሮ በሪ ሞዴል መንደር ፕሮጀክትን፣ የሶፊ ወረዳ የገጠር ሞዴል ቤቶች ግንባታን፣ የሐኪም ጋራ ኢኒሼቲቭ ሥራዎችን እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ፣ የክልሉ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሮዛ ዑመር፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ ሙክታር ሳሊህ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተው ለእንግዶቹ ገለጻ አድርገዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#አዲስ_አበባ #ኅዳር_20_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
