የሳይበር ደኅንነት ለሀገር ሉዓለዊነት

16

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር በ5ኛው ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ በተለያዩ ዘርፎች ሲያሠለጥናቸው የነበሩ ሠልጣኞችን አስመርቋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ ኢትዮጵያ የራሷን የዲጂታል የወደፊት እጣፈንታዋን የምትወስነው ባላት የቴክኖሎጂ ዕድገት ብቻ ሳይኾን ዕውቀት፣ ክህሎት እና ብቃት ነው ብለዋል።

የሀገር ሉዓላዊነት በቴክኖሎጂ በሰው ኀይል እና በፈጠራ የታገዘ መኾን ስላለበት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር በትኩረት እየሠራበት እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በ5ኛው ዙር የሳይበር ታለንት ሥልጠና የተመረቁ 1ሺ 140 ተማሪዎች የዚሁ ማሳያ መኾናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ ለሀገር የወደፊት የዲጂታል ጉዞ ተስፋ ናቸው ነው ያሉት።

ተመራቂዎች የተማሩትን ወደ ተግባር መፍትሔ እና ፈጠራ በመቀየር የሀገርን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የበኩላቸውን እንዲወጡም አደራ ብለዋል።

ሠልጣኞቹ በስድት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ዘርፎች ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ገልጸዋል።

የታለንት ልማት የጋራ ኀላፊነት በመኾኑ ሁሉም በጋራ ሊሠራ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት በመላው ሀገሪቱ ባሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

የሰውን ልጅ በብዙ መልኩ የሚቀይረውን ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ መጠቀም እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።

ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት ምህዳሩን በፅኑ መሠረተ ላይ ለመገንባት መሰል የታለንት ሥልጠናዎችን ማጠናከር ያስፈልጋልም ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቁ የሳይበር ደኅንነት ባለሙያን ለማፍራት እየሠሩ መኾኑንም ገልጸዋል።

በምርቃት መርሐግብሩ ላይ የተመራቂ ተማሪ ወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

✍️ ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_19_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“3.86 በህይወቴ ትልቅ ትርጉም ፈጥሮ ህይወት ለማዳን አዘጋጅቶኛል” የሜዳሊያ ተሸላሚዋ ተመራቂ ዶክተር እጹብ ስንታየሁ