
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት 7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
የምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችንም እያቀረቡ ይገኛሉ፦
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የተገኙ የጋራ ምክረ ሃሳቦችን ወደ ተጨባች ውጤት ለመቀየር መንግሥት ምን ዝግጅት አድርጓል?
የኢትዮጵያን የ2050 ራዕይ እና የመደመር መንግሥት ስትራቴጂ ዘርፎችን አሥተሳስሮ ለመተግበር ምን እየተሠራ ነው?
የሻዕቢያ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ግጭቶችን ለመፍጠር ተደጋጋሚ ይሠራል ለዚህ ጉዳይ መንግሥት የፖሊሲ አቋሙ ምንድን ነው?
የሀገሪቱን ሰላም በጠንካራ የሕግ ማስከበር ለማጽናት ለቀጣይ ምን ታቅዷል?
መንግሥት ጤናማ እና ፍትሐዊ የኾነ የገቢ አሠባሠብ ሥርዓትን በመዘርጋት የታክስ ግብን እውን ለማድረግ ምን አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው?
ብልሹ አሠራርን ለመግታት እና ጥብቅ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምን እየተሠራ ነው?
የኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ከመቅረፍ እና መረጋጋትን ከማረጋገጥ አንጻር ምን ፋይዳ አመጣ? እዳ የመክፈል አቅም ምን ላይ ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
