አፍሪካውያንን ያሰባሰበው ጉባኤ በአዲስ አበባ 🇪🇹

3

“የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት ከጤና ጥገኝነት እና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነት እና ጽናት የሚደረግ ሽግግር ” በሚል መሪ መልእክት የሚከናወነው አምስተኛው የአፍሪካ ኅብረተሰብ ጤና ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል::

የጉባኤው ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፦

✍️ የጤና ሉዓላዊነት እና ራስን መቻል፦ ከውጭ እርዳታ እና ጥገኝነት ወደ አፍሪካውያን-መር ፋይናንስ፣ አስተዳደር እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሸጋገር።

✍️ የሀገር ውስጥ ምርት፦ የክትባቶች፣ የመድኃኒቶች፣ የምርመራ መሣሪያዎች እና የሕክምና ቁሳቁሶች የሀገር ውስጥ ምርትን ማስፋፋት።

✍️ ዲጂታል ጤና እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፦ ዲጂታል ሽግግርን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዙ የጤና ሥርዓቶችን እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤን ማሳደግ።

✍️ የወረርሽኝ እና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም፦ የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥን፣ የወረርሽኝ ዝግጁነትን እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ማጠናከር።

✍️ ዓለም አቀፍ የጤና አስተዳደር፦ በዓለም አቀፍ የጤና መዋቅር ማሻሻያዎች ውስጥ የአፍሪካን ድምፅ ማሳደግ።

👉 እነማን ይሳተፋሉ?
‎
‎የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የየሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ የጤና ባለሙያወች፣ ተመራማሪወች፣ ወጣቶች፣ ፖሊሲ አውጭወች እና ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል።

‎ከ30 ሺ በላይ ከአፍሪካ እና ከሌላው የዓለም ክፍል የተሰባሰቡ ተሳታፊዎች ስለ አፍሪካ ጤና ሊመክሩ አዲስ አበባ ከትመዋል።
‎
ከአሁን በፊት የመጀመሪያው በኦንላይን ከተደረገ በኋላ ያለፉት ሶስት ጉባኤወች ሩዋንዳ፣ ዛምቢያ እና ደቡብ አፍሪካ ተከናውነዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን የአህጉሪቱ ወሳኝ መድረክ ያዘጋጀች አራተኛዋ ሀገር ናት።

#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
‎
‎#Africa #CPHIA2026
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_14_2019_ዓ_ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ቢዮ ጋር ተወያዩ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ።