
በሰሜን ሸዋ ዞን ከ125 ቢሊዮን 576 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 1 ሺህ 793 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በግንባታ እና በማምረት ሥራ ላይ መኾናቸውን የዞኑ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታውቋል።
በመምሪያው የፕሮጀክት ክትትል፣ ድጋፍ እና የኢንዱስትሪ ዞን ልማት ቡድን መሪ ትዕግስት ይገዙ እንደገለጹት ፕሮጀክቶቹ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በንግድ እና በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው።
የዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እና ውጤቶች፦
👷🏾♂️ የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ 74 ሺህ ለሚጠጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
🛣️ የመንገድ መሰረተ ልማት፦ ከባለሀብቶች እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በ121 ሚሊዮን ብር ወጪ 49 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ተገንብቷል።
⚡ የኀይል አቅርቦት፦ በ162 ሚሊዮን ብር ወጪ 6 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመር ተዘርግቷል።
⚠️ የመሬት አሥተዳደር እርምጃ፦ መሬት ወስደው ባላለሙ 170 ባለሀብቶች ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፣
❌ የ26 ያላለሙ ፕሮጀክቶች 184 ሺህ 066 ሄክታር መሬት ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓል።
🎯 በ2019 በጀት ዓመት 20 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ማምረት ሥራ ለማስገባት እና ከወጪ ንግድ ምርቶች ከ57 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም ቡድን መሪዋ ገልጸዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደብረ_ብርሃን #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም
✍️በፋንታነሽ መሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
