‎የባሕር በር ከሉዓላዊነት እስከ የሀገር ደኅንነት ዋስትና!

0

‎የባሕር በር ባለቤት መኾን ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሉዓላዊነት እና የብሔራዊ ደኅንነት ዋስትና ማረጋገጫ ነው፤ ውጫዊ ጥቃቶችን እና ሕገ ወጥ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከልም ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው።
‎
‎ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤት እስከነበረችበት ጊዜ ድረስ የባሕር ኀይልን ጨምሮ የራሷን የሉዓላዊነት እና የደኅንነት ዋስትና በማረጋገጥ ረገድ ጠንካራ አቋም ነበራት።

“የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ፦ መብቶች፣ ተጨባጭ ሁኔታዎች እና ዕድሎች” በሚል የተዘጋጀው ጥናት እንደሚያሳየው ከኾነ ግን የኢትዮጵያ የባሕር በር ማጣት ብሔራዊ ደኅንነቷን እና ክልላዊ ተፅዕኖዋን ተፈታትኗል።
‎
‎ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የባሕር ኀይል ባለቤት አለመኾኗ የንግድ መሥመሮቿን ራሷ እንዳትጠብቅ እና በቀይ ባሕር ጸጥታ ላይ ተፅዕኖ እንዳታሳድር አድርጓታል።

ለዚህ ማሳያው ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሕገ ወጡ የሕወሃት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከት በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ መጠን ያለው ትጥቅ ከጠላት ሀገራት በምጽዋ ወደብ በኩል መተላለፉን ማረጋገጣቸው ነው።
‎
‎የባሕር በር ዘላቂ ሰላምን እና ጸጥታን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው።

የባሕር በር ባለቤት መኾን የንግድ መሥመሮችን በቀጥታ በመቆጣጠር በውጭ ኀይሎች የሚደረጉ ፖለቲካዊ ጫናዎችን ለመቀነስ፣ የዲፕሎማሲ ድርድር አቅምን ከፍ ለማድረግ እና የሀገርን ጸጥታ እና ጂኦፖለቲካዊ መረጋጋት በዘላቂነት ለማጽናት ያስችላል።
‎
‎በድምሩ የባሕር በር ለሀገር ሰላም እና ጸጥታ መረጋገጥ የውጭ ሥጋቶችን የሚመክት ጋሻ፣ የኢኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጫ እና የሉዓላዊነት ምሽግ በመኾን ታላቅ ሚና ይጫወታል።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#Ethiopia_Sea_Access#National_Security #AMECO
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም
‎
‎✍️ በስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ታላቁ ሩጫ የአዲስ አበባ ሰፋፊ ጎዳናዎች እና አዳዲስ ገጽታዎች ዳግም ለዓለም የሚተዋወቁበት ልዩ መድረክ ነው” የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ