‎የኢትዮጵያ መከላከያ የሕልውና አምድ፣ የሴራ ማክሸፊያ ምሽግ እና የሰላም ማማ!

3

‎የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትውልድ ትውልድ ሲሻገር የመጣውን የድል አክሊል በትከሻው አዝሎ፣ የታሪክ አውድማዎችን በድል አድራጊነት የጨበጠ የማይበገር የሰላም ማማ ነው።

‎‎የድል ሠራዊቱ በየዘመኑ የተጋረጡበትን የውጭ ጠላቶች እና የውስጥ አሸባሪዎች እብሪት በብቃት በመደምሰስ፣ የኢትዮጵያን ሕልውና በማስቀጠል ረገድ የሀገር ፍቅር እና የጀግንነት ጥግ ያሳየ ሕያው ምሽግ ኾኖ ቆይቷል።

‎‎በፈተናዎች ማዕበል ውስጥ አልፎም በጸና ቁመናው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ አውለብልቧል። ይህ የጸና አቋም በዘመቻዎች እና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ጭምር የጀግንነት ታሪክ እንዲጽፍ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ መኾኑን በአህጉር እና በዓለም አቀፍ መድረኮች እንዲያስመሰክር አድርጎታል።

‎‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ሠራዊቱ የሀገርን ሕልውና እና ዳር ድንበር በማስጠበቅ፣ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ረገድ በጽናት እና በጀግንነት ታላቅ አርዓያ የኾነ ነው።

‎‎የኢትዮጵያን ነፃነት እና ታሪካዊ ኩራትም በተግባር አስመስክሯል። ይህ ሠራዊት ጠላትን መክቶ ከመመለስ ባለፈ ሀገርን ለሁለንተናዊ ከፍታ፣ ለሰላም እና ለብሩህ ዕድገት የሚያበቃ ጠንካራ አቅም ያለው የድል ሠራዊት መኾኑንም ጠቁመዋል።

‎‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መከላከያ ሠራዊት ያለውን ሰላም እንዳይደፈርስ የሚጠብቅ፣ የጠፋን ሰላም ለማምጣት የሚተጋ፣ የመጣ ሰላምን ለማጽናት የሚሠራ፣ ዋነኛ ዓላማውም ሰላምን ማስፋት እና የሀገር ብልጽግናን ባልተቋረጠ መንገድ እውን ማድረግ ብቻ ነው በማለት ተናግረዋል።

‎‎በተቀናጀ ራዕይ እና ቁርጠኝነት የሚመራው መከላከያ ሠራዊት ዛሬም በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የተደቀኑትን የጥፋት አጀንዳዎች እና የጠላቶችን ሴራ በጽናት እያከሸፈ፣ የትናንት አኩሪ ታሪኩን በብሩህ ተስፋ እየደገመ ይገኛል።

‎ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ክብር ከፍ አድርጎ ለማስቀጠል በተሰለፈባቸው ግንባሮች ሁሉ አሸናፊነቱን በታሪክ መዝገብ ላይ በደማቅ ቀለም እየጻፈ ይገኛል።

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎‎#AMECO #Proud_Of_ENDF #EthiopianSovereignty #Ethiopia

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_11_2019_ዓ_ም

‎✍️ በስማቸው አጥናፍ

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article‎ኢትዮጵያን የዓለም መዳረሻ እያደረጉ የሚገኙት የቱሪዝም እመርታዎች!